Biography

የአምባሳደር ዘውዴ ረታ አጭር የሕይወት ታሪክ

ዘውዴ ረታ በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር ነሐሴ 7 ቀን 1927 ዓ.ም አዲስ አበባ ተወለደ

ከ1033 እስከ 1945 ዓ.ም ቀድሞ ደጃዝማች ገብረ ማርያም ይባል በነበረውና ኋላ ሊሴ ገብረማርያም ተብሎ በተሰየመው የፈረንሣይ ትምህርት ቤት የመጀመሪያውንና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን አከናውኗል፡፡

  • ከ1945 እስከ 1948 ዓ.ም በጋዜጣና ማስታወቂያ መሥሪያ ቤት የቤተመንግሥት ዜና ጋዜጠኛና በራዲዮ ዜና አቅራቢ
  • ከ1948 እስከ 1952 ዓ.ም በፓሪስ የጋዜጠኝነት ሞያ በማጥናት በዲፕሎማ ተመረቀ
  • ከ1952 እስከ 1954 ዓ.ም የኢትዮጵያ ድምፅ ጋዜጣና የመነን መጽሔት ዲሬክተር
  • ከ1954 እስከ 1955 ዓ.ም የኢትዮጵያ ሬዲዮ የብሔራዊ ፕሮግራም ዲሬክተር
  • ከ1955 እስከ 1958 ዓ.ም የኢትዮጵያ ወሬ ምንጭ ዋና ዲሬክተር
  • ከ1958 እስከ 1960 ዓ.ም የማስታወቂያ ሚኒስቴር ረዳት ሚኒስትር
  • ከ1960 እስከ 1962 ዓ.ም የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ድርጅት ዋና ሥራ አስኪያጅ
  • ከ1956 እስከ 1962 ዓ.ም የፓን አፍሪካ ኒውስ ኤጀንሲ ማኅበር ፕሬዚዳንት
  • ከ1962 እስከ 1967 ዓ.ም ወደ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ተዛውሮ
  1. በፓሪስ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ሚኒስትር ካውንስር
  2. የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ም/ሚኒስቴር
  3. በሮም እና በቱኒዚያ የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት አምባሳደር ሆኖ ሠርቷል

በጠቅላላው በቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ዘመነ መንግሥት የሀያ ሁለት ዓመታት አገልግሎት ካበረከተ በኋላ በደርግ ዘመን ከ1967 ዓ.ም ጀምሮ ስደተኛ ሆኖ በአውሮፓ በቆየበት ዘመን በሮም የኢንተርናሽናል ድርጅት ውስጥ (IFAD) ለአሥራ ሦስት ዓመታት በፕሮቶኮልና በመንግሥታት ግንኙነት ጉዳይ ኃላፊ ሆኖ ሠርቷል፡፡

በ1959 ዓ.ም ጋብቻውን መሥርቶ ከሕግ ባለቤቱ ከወይዘሮ ገሊላ ተፈራ ጋር ሦስት ልጆች አፍርተው ይኖራሉ፡፡ ከንጉሠ ነገሥቱ መንግሥት የምኒልክ የመኮንን ደረጃና የኢትዮጵያ የክብር ኮከብ አዛዥ መኮንን ኒሻን ተሸልሟል፡፡ እንዲሁም ከአፍሪካ ፣ ከእስያና ከአውሮፓ በድምሩ ከሀያ ሁለት አገሮች የታላቅ መኮንን ደረጃ ኒሻኖች ተሸልሟል፡፡ ከዚህ ቀደም በ1945 እና በ1946 ዓ.ም ካዘጋጃቸው አራት ቲያትሮች ሌላ ፤ በ1992 ዓ.ም የኤርትራ ጉዳይ በ1997 ዓ.ም ተፈሪ መኮንን በቅርቡም የቀድሞ ኃይለሥላሴ መንግሥት የተሰኙትን መጻሕፍቶች ጽፏል፡፡